Tamiratjinka
የአብርሃም ልጆች ለ400 አሜት በግብጽ በባርነት እንደነበሩ ይታወቃል። የራሳቸው ባልሆነ ሀገር የምደክሙ የሚለፉ ጡብ እየረገጡ የሰው ከተማ የሚገነቡ ለባርነት የተወሰኑ ነበሩ።
ከብዙ አመታት በኋላ እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባውን ቃልኪዳን አሰበ። ከግብጽ ባሪነት በብዙ ተዓምራት አስወጣቸው። ሀብት ንብረታቸውን ይዘው ከባርነት ቀንበር ተላቀው ወደ ተስፋይቱ ምድር መጓዝ ጀመሩ።
ምድረበዳ ላይ ረሀቡ፣ ጥማቱ፣ ድካሙ ስበረታ የእሥራኤል ልጆች በሙሴ ላይ አመጹ። "ግብጽ ይሻለን ነበር። ጡባችንን እየረገጥን እዚያው በተቀበርን ነበር" አሉ። መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚናገረው ከግብጽ ከወጡ አባቶች ኢያሱና ካለብ ስቀሩ ሁሉም በምድረበዳ አለቁ። የተስፋይቱን ምድር አላዩአትም። በምድረበዳ የተወለዱ ግብጽን የማያውቋት ልጆች ከካለብና ኢያሱ ጋር ርስታቸውን ወረሱ።
ለምን ይኸንን ታርክ አነሳሁ?
የሰው ልጅ የገጠመውን ፈተና እያለፈ እያሸነፈ ወደፊት እንጂ ወደኋላ ማሰብ የለበትም። ወደኋላ ማሰብ ፍጻሜን ያበላሻል።
ኢትዮጵያ አሁን ለገጠማት ችግር መፍትሄው ወደፊት መጓዝ ነው። የትላንቱን የባርነት ኑሮ ከገጠመን ችግር አንጻር ማስተያየት ተገቢ አይደለም። በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊ ሥርዓቷ የበለጸገች ኢትዮጵያን በራዕይ አይተናል። አልመናል።
መንገድ ላይ ለሚገጥመው መሰናክል ሁሉ እጅ የሚሰጥ ሰው ያለመውን አይጨብጥም