ይሄን ልጅ ወደድኩት መሠለኝ ብዬ አንደቀልድ ለራሴ ነግሬው ነበር አነደሱ ያሉ መልከመልካም ብዙ አላየሁም እንዴ አይቻለሁ እንጃ ግን ማንንም ልብ አላልኩም አልመረጥኩም ከማንም በላይ መረጥኩት እና ለትንሿ ልቤ ሲያቅፈኝ ሲስመኝ አይኔን ሲያየኝ ሳሳሁላት ለራሴ አዘንኩ ያቺን ሰሞን ፍቅር ስለያዘኝ ከፋኝ አንጂ በድጋሚ አይኖቼ ብዙ ወንዶች ያያሉ እንጂ ማንንም ልብ አላልኩም የእሱ ፍቅር አዲስ ሰው አደረገኝ ከእሱ በኋላ ለራሴ ያለኝ ዋጋ ጨመረ ስለመረጠኝም ደስ አለኝ አቤት ስወደውውው....ሁሉ ነገሩ ደስ ይለኛል ሰው ስለሱ ሲያነሳ አልወድም በክፉም ሆነ በጥሩ አንዲያነሱት አልፈልግም ብቻዬን ነው ልወደውም ልጠላውም የምፈልገዉ ከሱ በኀላ አልወድም ማለት አልፈልግም እንጂ ቢሆንልኝ ደስ ባለኝ እንደማይቆይ እያወኩት ሌላው ቢቀር የመቆየት ሀሳብ ቢኖረው ሰፍሳፋነቴ እንደማያቆየው አውቅ ነበር ፡፡ ስ..ፍ..ስ..ፍፍፍ አልኩለት፡፡ አጉል አስለምዶኝ ሰምሮልኝ እንኳን ከወራት የዘለለ አብሮኝ ሳይቆይ በቅጡ ሳንተዋወቅ አበቃ ፡፡ ከተቻለ በሌላኛው የህይወት አጋጣሚዎች ከተገናኘን የምናስቀጥለው ወይ ከዚህ የተሻለ መቋጫ እናበጅለታለን፡፡ ቢኖርም ባይኖርም እወደዋለው ምንም አይመስለኝም አልተጎዳሁም ማለት እፈልጋለው ግን ልቤን ስንጥቅ አድርጎኝ የሚወርድ የማላቀው ስሜት አለ ብቻ ጥልኝ፡፡All Rights Reserved
1 part