የስብሃትን መጽሃፍ አነበብኩ (ለአራዳዎቹም ለፋራዎቹም የጻፈውን)፤ እራሴን ከየትኛው እንደምመድበው ባላውቅም ቅሉ ያንን ለማወቅ እንደሱ በየኮማሪ ቤት እየዞሩ ወሬ መቃረም ግን አላስፈለገኝም ምክንያቱም ለጊዜው ስሙን የማልጠቅሰው 'የቀለም ደጃች-ዉቤ ሰፈር' /ትክክለኛውን አይደለም/ ምን ያልተፈፀመ ነገር አለ? ሊያውም በጠራራ ፀሃይ መቼም የሱን የስነ-ፅሁፍ ችሎታ ቅንጣት ታክል ባይቸረኝም እዛ ሃይስኩል የተፈፀመውን፣ የተወራውን፣ በሚገርም ብልሃት ታቅዶ የቀን ቅዠት ሆኖ መና የቀረውን፣... እንደወረደ ማሳሰቢያ:- ታሪኩ ፆታዊ ትዕይንቶችን እና ከመደበኛው ወጣ ያሉ አስተሳሰቦችን፣ መረን ያጣ የጎረምሳ ንግግር እንደሚያካትት እወቀው፤ ... በተረፈ ጥቁሩ-ፈጣሪ ይከተልህ * * * ለመወሰን እዲረዳዎ፣ የእውነት የሆነው:- ዛክ ሲበዛ ደብቶታል፤ ያ ውስጡ የሚራወጠው የበፊቱ ግለት ጠፍቶ በዛ የመኸር ወር ውስጡ እንደበረዶ ቀዝቅዟል። ... ፊትለፊት ጸደንያ (ጸዲ-ቬዱ) ስትመጣ ከርቀት ተመለከታት። በትንሹ ታነክሳለች። ህመም እየተሰማት እንደሆነ ቅጭም ያደረገችው ፊቷ ያሳብቃል። ወደእርሱ ስትቀርብ የጨፈገገው ፊቷ ተፈቶ በምትኩ በፈገግታ ተሞልቶ አበራ። ፊቷ እንደበራ አጠገቡ ደረሰች፣ "ቬዱ ምነው?" ሲል ለመጠየቅ ያክል ጠየቃት፤ ምላሷን አሹላ ወደውጪ አውጥታ የላይኛውን ከንፈሯን አስነክታ እየተቆላች ስቃ ስታበቃ "በዱኝ" አለችና ከት ብላ