ሴት

278 18 6
                                    

ብላ አለችው በልታ ፤ አሳተችው ስታ፣

የ እባቡን ሰምታ፣

ታሪክ ጨነፈገ ፤ ፍጥረት ተረገመ፣

ገነት ተከርችሞ ፤ ሲኦል ተከተመ፣

የወጣው ላይገባ ፤ በስልጣን ታተመ፣

በእሳት ሰይፍ አጠራት ፤ ሱራፊን አቆመ፣

ዘመንም ዘመነ አምስት ሺህ ሆነ፣

እንዝርትዋ ውስጥ ገባ አለም ተሸመነ፣

በሴት ምክንያት ጠፋ ፤ በሴት ምክንያት ዳነ፣

ሔዋንን ያሳተው ፤ በማርያም ልጅ ሞተ።

Ethiopian PoemsWhere stories live. Discover now