እናት ማለት ሴት ናት፣
እናት ማለት ሀገር፣
ወልዳ የምታሳድግ ላቧን ጠብ በማድረግ፣
ለእራሷ እየተወች ለልጇ የምትሰጥ፣
የ እርሱ ህይወት ከእርሷ እንዲሻል ተግታ ለመለወጥ፣
እናት ጀግና ናት የ ልጇ አርበኛ፣
ኮትኩታ አሳዳጊ የ ፍቅር መገኛ፣
ኑሪ እናት ዓለም ለዘለዓለም ኑሪ፣
ፈጣሪ አያሳጣሽ ጠዋሪ ቀባሪ፣
እባካችሁ ሰዎች ኧረ እንለምናችሁ፣
እናትህ እንዲህ ትሁን ማለት ይቅርባችሁ፣
ዘጠኝ ወር ተሸክማ ላሳደገች እናት፣
በ እውነት እንዲህ መሰደብ መቼም አይገባት፣
ምን አረገች እርሷ ከመውለድ በስተቀር፣
ለፍታ በማሳድግ ላቧን ጠብ በማድረግ።
እናት ብር ሆና እኔ ብበደራት፣
ዘለዓለም ተንከባክቤ በእቅፌ ባቆያት።
