መከራ ሳይነካው ችግር ሳይዳብሰው፣
ማነው በዚህች አለም ደልቶት የሚኖር ሰው፣
የዚህች አለም ኑሮ ውስጡ ብልጭልጭ ነው፣
ያገኘው ሲደሰት ያጣው ሲበሳጭ፣
ቢወፍር ዱባ ሲቀጭጭ ትንኝ፣
ሲናገሩ አፈኛ ዝም ሲሉ ሞኝ።
