ገና

151 11 5
                                    

ገና ነው ከበዓሎች አንዱ ዋና፣
የዓለም መድኃኒት መወለድ አረገው ቀኑን ገናና፣
ከ ቅድስተ ቅዱሳን ንፅህተ ንፁሃን፣
ተወለደ ጌታ ለዓለም መዳኛ።

ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ፣
ማን አለ እንደ እርሷ እሙ ለአዶናይ፣
የቴክታ በጥሪቃ የህልማቸው ፍቺ፣
ማርያም ድንግል ናት ለትውልድ ተስፋ ሰጪ።

መልአኩ ተልኮ ከእግዚአብሔር አብ፣
አበሰራት እሷን በሳድሱ ወር፣
ይሁንልኝ ብላ የገብርኤን ሰላምታ፣
ወለደችው እሷ የዓለሙን ጌታ።

በኢየሩሳሌም በቤተልሄም፣
በበረት ተኝቶ ሳለ ቅዱሱ ህፃን፣
ልብስም አልለበሰ ነበር ገላው እርቃን፣
እናቱ ባታገኝ ምታለብሰው ልብስ፣
እንስሳት አለበሱት ከበው የትንፋሽ ልብስ፣
አውቀዉታልና መድኃኒት መወለዱን፣
በ 29 ታህሳስ ወደዚህ ዓለም መምጣቱን።

ሰብዐ ሰገል እነዛ ጠቢባን፣
ሊሰግዱም መጡ ለአምላከ ባህራን፣
ተመርተው በኮከብ እዛው እንደደረሱ፣
ከእረኞቹ ጋራ መሬት ላይ ወደቁ እጅንም ሊነሱ።

እነዛ ጠቢባን አመጡ እጅ መንሻ፣
ለህፃኑ ንጉስ ለዓለሙ ጌታ፣
ወርቅ ለክብሩም ለልዑል ጌትነቱ፣
ዕጣን ለክህነት ከርቤውን ለሞቱ፣
አምጥተዉለት እንደታዘዙት ወደ አገራቸው ወዲያውኑ ተጓዙ።

ቤዛ ኲሉ ዓለም ተወልደ ዮም፣
ሰውና መላእክት አመሰገኑት፣
ቤዛ ኲሉ ዓለም ተወልደ ዮም፣
ሰውና መላእክት አመሰገኑት።

Author's Note

                   This Is Something that I Wrote To Present At School When We celebrated Christmas. I Only Wrote It In Almost Two Days But I'm Proud Of It. And I Probably Would've Published This Earlier But I Got Lazy and It's A Little Harder To Type In Amharic Than In English. Anyways I Hope You like It.

You've reached the end of published parts.

⏰ Last updated: Apr 20, 2020 ⏰

Add this story to your Library to get notified about new parts!

Ethiopian PoemsWhere stories live. Discover now